መግለጫ

የኢትዮጵያዊነታዊ ድርጅቶች የጋራ መድረክ

በማርች 29፣ 2023 በሰሜን አሜሪካን የሚገኙ ስማቸዉ ከዚህ በታች የተመለከተዉ የሲቪክ ድርጅቶች እና የኢትዮጵያዋን
ተቆርቋሪ ስብስቦች በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸው አካል በጋራ በመመስረት አገሪቱ ለገባችበት አደገኛ የስርዓት ቀውስ እና
የህልውና አደጋ ተጠያቂ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ እና የሚያራምደው እኩይ የሆነ የአገዛዝ ስርዓትን በሰላማዊ
ትግል ለመታገልና ስርአታዊ ለዉጥን ግብ አድርጎ ኢትዮጵያን ለመታደግ የሚሰራ የጋራ መድረክ መስርተዋል።
1. እምቢልታ/አገር አድን ኅብረት
2. ግሎባል አሊያንስ(GLOBAL ALLIANCE FOR THE RIGHTS OF ETHIOPIAN
3. የኢትዮጵያ የውይይት እና የመፍትሄ መድረክ(EDF)
4. ቪዥን ኢትዮጵያ (VISION ETHIOPIA)
5. የዲሲ ግብረ ሃይል
6. የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማእከል(CREW)
7. አለምአቀፍ የኢትዮጵያዉያን የሲቪክ ድርጅቶች ኔትወርክ (WE CAN)
8. ልዩ ልዩ የኢትዮጵያዋን ተቆርቋሪ ስብስቦች (concerned Ethiopians)

ድርጅቶቹ በኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ እየተከሰተ ያለውን የአገሪቱ ህልውናን አደጋ ላይ የጣለ ሁኔታን በመገምገም የኢትዮጵያ ህዝብ
ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ መብቶቹ እንዲከበሩለት ለመታገል በአራት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ የጋራ ራዕይ በመንደፍ
በሚከተሉት መሰረታዊ ችግሮች ላይ አብረው ለመስራት ስምምነታቸውን አስፍረዋል።
1. ኢትዮጵያ ብዙ ባህል ያለባት የአንድ ህዝብ አገር ስትሆን ለረጅም ዓመታት አገረ መንግስት የመስረተች ታሪካዊት እና ታላቅ
የማትከፋፈል አገር ናት። ይህ አንድነታችን የማንደራደርበት ኣቋማችን ነው።
2. የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና ልኡላዊነት የማይደፈር መሆን አለበት።
3. ሁሉም ኢትዮጵያውያን ነጻ ዜጎች ሆነው በአገሪቱ በማንኛውም ስፍራ በእኩልነት የመኖር መብት ሊኖራቸው ይገባል።
4. ኢትዮጵያ በታላቅ የህልውና ጥያቄ ላይ ገብታለች። አገረ መንግስቱ ለሰላሳ ዓመታት በጸረ ኢትዮጵያ ጠባብ ቡድኖች አመራር
በመውደቁ የተነሳ በሙስና፣ በአድልዎ እና በፍትህ አልባ አሰራር በመበከሉ ታይቶ የማይታወቅ ኢሰብአዊ ግፍ በህዝቧ ላይ
እየተፈጸመ ነው። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ሰፍኖ ያለው የጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ መንግስት እና ስርዓት አገሪቱን ወደ
ሰላም፣ ዲሞክራሲ እና ብልጽግና ሊወስዳት የማይችል በመሆኑ በምንም አይነት ሁኔታ መቀጠል የለበትም። ለእነዚህ እኩይ
አሰራሮች በዋናነት ተጠያቂ ስለሆነ ይህንን የጥቂት አምባገነኖች መንግስት የሚያራምደው ስርዓት እንዲያከትም ትኩረት
በመስጠት የዲሞክራሲያዊ የስርዓት ሽግግር ላይ በጋራ በአቋቋሙት መድረክ አማካይነት ለመታገል ተስማምተዋል።
በማከልም በእነዚህ አራት ነጥቦች ላይ የሚስማሙ የሲቪክ ድርጅቶች ሁሉ ይህንን ኅብረትና የጋራ መድረክ አባል እንዲሆኑ
ጥሪውን ያቀርባል።

The Forum of Ethiopianist Civic Organizations in the Diaspora
የኢትዮጵያዊነታዊ ድርጅቶች የጋራ መድረክ

The Forum:
The Forum is a coalition of rights-based and charitable Ethiopian civic organization in the
diaspora. The Forum is established for the sole purpose of articulating a shared vision for a
democratic and united Ethiopia and implementing a common and practicable strategy to support
full respect for human, civil, and political rights in Ethiopia. The Forum optimizes collaboration
around common projects and offers our collective voice to institutionalize a culture of respect for liberty,

freedom, and the rule of law. The Forum is inclusive and honors the principles of non-
violence and rights that are enshrined in international treaties and conventions governing a free
society.

Membership:
Any legally registered CSO is eligible for membership provided it accepts the following four core
principles, which are articulated in The Citizens Charter for a Democratic Ethiopia. Other
types of membership (such as associate membership by individuals and coalitions) will be
specified in the bylaws:

1. Ethiopia is a multicultural country, but its people are indivisible under the tricolor.
2. The sovereignty of Ethiopia is sacrosanct, and its territorial integrity is non-negotiable.
3. Every Ethiopian is entitled to equal rights and responsibilities that define free citizenship.
4. Ethiopia, in order to survive, must extricate itself from the toxic trap of constitutionalized
identity politics by launching a “democratic transition,” including an orderly dissolution of
the Prosperity Party and its discredited leadership.

Objectives and Goals:
The Forum commits itself to timely and practical projects, including:
1. Advocacy for Justice and the Rule of Law: Gather credible evidence on the violation of
citizen rights with impunity and bring the perpetrators to international justice. The
violations include genocidal political violence and ethnic cleansing (which especially
targeted the Amhara), war crimes, government orchestration of civil conflict, willful
disregard for the welfare of distressed communities, stifling of basic freedoms of mobility
and speech to advance polarization of society, and institutionalized corruption.
2. Campaigns and Civic Engagement: Conduct relentless campaigns of non-violent civic
resistance against the ethnocentric dictatorship, including targeted economic sanctions
and boycotts.
3. Relief and Rehabilitation: Provide relief assistance to the millions of victims of political
violence, atrocity crimes, and natural disasters in a coordinated and effective manner.
4. Democratic Constitutional Order: Mandate a taskforce to craft a workable roadmap of
political transition to a democratic constitutional order for consideration by the Ethiopian
people and their legitimate organizations.

Adopted by the founding members of the Forum on March 29, 2023.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Fill out this field
Fill out this field
Please enter a valid email address.
You need to agree with the terms to proceed

Menu